Sayat Demissie Instagram – አንዳንድ ሰው አለ ከጣና ‘ሚሰፋ
–
.
ካባይ የሚጋፋ
ከዋርካ ‘ሚፋፋ።
አንዳንድ ሰው አለ ሁሉ የሚሰጠው
ሁሉ ‘ሚጨብጠው
ሁሉ ‘ሚያዳምጠው።
አንዳንድ ሰው አለ
አንድ ቦታ በቅሎ ለሁሉ ‘ሚበቃ
ሁሉን የሚያነቃ
ሁሉን የሚያበቃ።
አንዳንድ ሰው አለ የሁሉ ማረፊያ
ሁሉን መደገፊያ
ሁሉን መታቀፊያ።
በዘመናት መሐል ድንገት ተከሥቶ
ለሰው ሁሉ ታይቶ
ያንን ዘመን ዋጅቶ
ፈጣሪ መኖሩን ለሰው አመልክቶ
ወደላይ የሚሄድ ከወደ ላይ መጥቶ።
አንዳንድ ሰው አለ….. Daniel kiberete .
ክቡር ተቀዳሚ ሙፍቲህ የጸሎት መርኀ ግብር ላይ እንዲህ አሉ፡- “ዱአ አድርግ ስትሉኝ ‘አይኾንም’ ያልዃችሁ ወንድሞቻችን የኦርቶዶክስ አባቶች ሲጸልዩ ኹላችንም ቁመን ‘አሚን!’ ብለናል። ያ ጸሎት በቂ ነው ብዬ እንጂ ለሌላ አይደለም፤”. @rekikyami 🙏 | Posted on 09/Apr/2020 02:16:02


