Rgat Afewerki Ybrah Instagram – ፈጣሪ አምላኬ ይቅር በለኝ ዛሬ ህግህን ሳፈርሰው
አትፍረድ ብትልም እኔ ግን አልቻልኩም ፈርዳለው በዚህ ሰው።
የክፋትን ጥጉን የመቆሸሽ ጥጉን ገደቦች ላለፈ
ያንዲት ምስኪን ህፃን ክብሯን በግፍ ገፎ ነፍሷን ለቀጠፈ
የእጁን እንዲያገኝ ስቃይ እና ሞቱን ለሱ መመኘቴ
የጨቅላዋን ህመም ማሰብ ቢያቅተኝ ነው ባይችል ነው አንጀቴ
የቆሰለ ውስጧን የእናቲቱን እምባ ሚያብሰው ሲጠፋ
ፍትህ እየተዛባ ተበዳይ ሲበደል
ውስጣችን ቢከፋ
አቤቱ ፈጣሪ አነባን ወዳንተ
አነባን ወደላይ
ፍርድህን አሳየን ክፉዎች ቀጥተህ
በምድርና በሰማይ።
https://www.change.org/p/justice-for-heaven-and-her-mother?recruited_by_id=94947080-5cca-11ef-af3a-c38f3884f55d&utm_source=share_petition&utm_campaign=psf_combo_share_initial&utm_term=signature_receipt&utm_medium=copylink
👆 በዚህ ሊንክ በመግባት ፊርማችንን መስጠት የቻልን ደግሞ የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ እንችላለን።
#ፍትህለሔቨን
#Justiceforheven
✍️#BegitimEnawga | Posted on 19/Aug/2024 13:40:39



